መዝሙር
እቴ ሙሽራዬ
እቴ ሙሽራዬ
እቴ ሙሽራዬ ሰለሞን ያለሽ (2x)
እኔም ልበልሽ እናቴ እመአምላክ ግቢ ከቤቴ
እኔም ልበልሽ እናቴ ማርያም ግቢ ከቤቴ
ሁሉም ሰው ለራሱ ወንበር ሲዘረጋ
የክብር ሽልማት ለራሱ ሲያስጠጋ
ድንግል እንደ ባሪያ ውሃ ተሸክመሽ
ጌታን በትህትና ታገለግያለሽ
ነይ በደመና ( 4x ) እመቤታችን ርህይተ ህሊና
አዝማች…
ወርቀዘቦ ለብሰው በቤቱ ከሞሉት
በሀርና በእንቁ ከተንቆጠቆጡት
በሰው ፊት ያማሩ ብዙ ሆነው ሳለ
ጌታ ግን ወደደሽ እናቴ ነሽ አለ
ነይ በደመና (4x) እመቤታችን ርህይተ ህሊና
አዝማች …
አሳድጎሽ ሳለ መላኩ መግቦ
ተሸልመሽ ሳለ በዝቶልሽ ተውቦ
እጅግ በትህትና ስላገለገልሽው
እንደ ኪሩብ መላክ ጌታን ተሸከምሽው
ነይ በደመና (4x) እመቤታችን ርህይተ ህሊና
የባህራን ወዳጅ ሚካኤል ሲነሳ (2ጊዜ)
እኔም ልበልህ አባቴ ሚካኤል ግባ ከቤቴ (2ጊዜ)
ሰለስቱ ደቂቅን ያወጣህ ከእሳት (2ጊዜ)
እኔም ልበልህ አባቴ ገብርኤል ግባ ከቤቴ (2ጊዜ)
የዋሻው አንበሳ ተክልዬ ሲነሳ (2ጊዜ)
እኔም ልበልዎ አባቴ ተክልዬ ግቡ ከቤቴ (2ጊዜ)
ለእዘራ ያጠጣህ ጽዋሃ ህይወት (2ጊዜ)
እኔም ልበልህ አባቴ ኡራኤል ግባ ከቤቴ (2ጊዜ)