መጸሀፍ ቅዱስ
የድንግል ማርያም ስሞች
ስም ለፈጣሪም ሆነ ለፍጡራን ለመጠሪያነት ያገለግላል፡፡ ይህም ስም አንዱን ከሌላው ለይቶ የሚያሳውቅ የፍቅር መግለጫ ነው፡፡ በጽሑፍም ሆነ በቃል ማስተላለፍ የሚቻለው በስም አማካኝነት ነው፡፡ በብሉይ ኪዳንም ሆነ በሐዲስ ኪዳን እግዚአብሔር ለሚወዳቸውና ለመረጣቸው ሰዎች ስም ያወጣ እንደ ነበር ሁሉ፤ ሰዎችም ያወጡ መጠሪያ ይሰጡ ነበር፡፡ ይህም ስም የሚሰየመው ወይም መጠሪያ ሆኖ የሚሰጠው እንዲሁ በዘፈቀደ ሳይሆን መሠረታዊ ምሥጢርና ትርጉም አለው፡፡ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን «እስመ ስሙ ይመርህ ኀበ ግብሩ» በማለት ስም ግብርን ሁኔታን እንደሚገልጽ መሥክረዋል፡፡
የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች ምስክርነት ከስም አጠራሯ በመጀመር ለስመ ድንግል ማርያም ዘርፍ /ቅጽል/ አልያም ምትክ አድርገን የምንጠቀምባቸው ምሥጢራዊና ትርጉም ያላቸው ንጽሕናዋን፣ ቅድስናዋን፣ ድንግልናዋን፣ ወዘተ የሚመሰክሩ በርካታ ስሞች አሏት፡፡ ስለ እመቤታችን ስሞች ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ካላቸው ፍቅር የተነሣ አብዝተው፣ አምልተው፣ አስፍተው፣ አመስጥረው ከተረጐሙት ጥቂቱን እንደሚከተለው አቅርበናል፡፡
ምልዕተ ጸጋ፡- መጽሐፍ ቅዱስን ስናነብ ይህን ቃል ከእመቤታችን በቀር ለማንም እንዳልተነገረ እንረዳለን፡፡ አዳም ከፍጥረት ሁሉ አልቆ አግንኖ በአርአያውና በአምሳሉ የፈጠረው ፍጥረት ነበር፡፡ ነገር ግን በኃጢአት ምክንያት የተሰጠው ጸጋ ተገፈፈ፡፡ አብርሃም ወዳጁ ነበር፡፡ ዳዊትም እንደልቤ ያለው ነው ሙሴንም ከ570 ጊዜ በላይ ቃል በቃል አነጋግሮታል፡፡ በዘመነ ሐዲስም ሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ ጴጥሮስን «አንተ ብፁዕ ነህ» ብሎ መስክሮለታል ይሁን እንጂ እንዲህ ባለው ቃል እንደ እመቤታችን «ጸጋ የሞላብህ» «ጸጋ የሞላብሽ» የተባሉ ሌሎች አልተገኙም፡፡ እመቤታችን ከፍጥረት ሁሉ ተመርጣ ከእናቷ ማኅፀን ጀምሮ እግዚአብሔር የጠበቃት፣ ያደረባት «የከተመባት ረቂቅ ከተማ» መሆኗን መልአኩ በመሰከረበት ቃል «ምልዕተ ጸጋ» እያልን እንጠራታለን፡፡ ሉቃ.1-26፡፡ እመቤታችን የተለየች ናትና «ጸጋ የሞላብሽ» /የጸጋ ግምጃ ቤት/ ተብላለች፡፡
እምነ /«ም» ጠብቆ ይነበብ/ ጽዮን፡- እግዚአብሔር ወልድ ኢየሱስ ክርስቶስን አባት «አባታችን ሆይ» ብለን እንደምንጠራው ሁሉ ወላዲተ አምላክንም እናታችን ብለን እንጠራታለን፡፡ ማቴ.6-9፡፡ ቅዱስ ዳዊትም «እምነ ጽዮን ይብል ሰብእ፡ ሰው ሁሉ እናታችን ጽዮን ይላል» በማለት እመቤታችን አማናዊት ጽዮን መሆኗን አስረድቷል፡፡ መዝ.86-5፡፡
እምነ ጽዮን ማለት እናታችን ጽዮን ማለት ነው፡፡ በመጀመሪያይቱ የሰው ልጆች ሁሉ እናት ሔዋን አማካኝነት ከርስታችን ወጥተን መጠጊያ አጥተን ነበር በዳግማዊቱ ሔዋን በድንግል ማርያም ደግሞ ወደ ርስታችን ተመልሰናልና እናታችን ጽዮን እንላታለን፡፡ ጽዮን ማለት አንባ መጠጊያ ማለት ነው፡፡
መጽሐፍ ቅዱስም ድንግል ማርያምን ጽዮን በማለት ይጠራታል፡፡ ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳዊት «እግዚአብሔር ጽዮንን መርጦአታልና ማደሪያውም ትሆን ዘንድ ወድዶአታልና እንዲህ ብሎ ይህች የዘላለም ማደሪያዬ ናትና በዚህች አድራለሁ፡፡» መዝ.131-13፡፡ በማለት የተናገረው ትንቢት ፍጻሜ ልዑል እግዚአብሔር ከሴቶች ሁሉ ለይቶ ድንግል ማርያምን ለእናትነት የመረጣት መሆኑንና ማደሪያውም ትሆነው ዘንድ የወደዳት መሆኑን የሚያስገነዝብ ነው፡፡ መዝ.47-12፤86-5፡፡
መድኃኒታችን በዕለተ ዓርብ በቀራንዮ በመስቀሉ ላይ ሳለ ለፍቁረ እግዚእ ዮሐንስ «እነኋት እናትህ» በማለት በደቀ መዝሙሩ አማካኝነት እናቱን ድንግል ማርያምን ሥጋውን ለቆረሰላቸው ደሙን ላፈሰሰላቸው ምእመናን እናት ትሆን ዘንድ ሰጥቷታልና ከላይ እንዳየነው ጽዮን የድንግል ማርያም ስም ነውና ጌታችን እናት አድርጎ የሰጠንን እመቤት እምነ ጽዮን /እናታችን ጽዮን/ እንለታለን፡፡
እመ ብርሃን፡- እመ ብርሃን ማለት የብርሃን እናት ማለት ነው፡፡ «እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ» ያለውን ብርሃነ ዓለም /የዓለም ብርሃን/ መድኃኔ ዓለም ክርስቶስን የወለደች ናትና የብርሃን እናቱ /እመ ብርሃን/ ትባላለች፡፡ ዮሐ.8-22፡፡ ጌታውን ይወድድ የነበረና ጌታውም ይወደው የነበረ የከበረ ደቀ መዝሙር ቅዱስ ዮሐንስ «ለሰው ሁሉ የሚያበራው እውነተኛው ብርሃን ወደ ዓለም ይመጣ ነበር፡፡» በማለት የመሰከረለትን ጌታ በብሥራተ መልአክ በግብረ መንፈስ ቅዱስ አማናዊውን /እውነተኛውን/ ብርሃን ጌታችንን ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን ጸንሳ የወለደች በመሆኗ እመ ብርሃን እንላታለን፡፡ ሊቁ «እመ ብርሃን አንቲ ነዓብየኪ በስብሐት ወበውዳሴ፡- አምላክን የወለድሽ እመቤታችን ሆይ የብርሃን እናት ነሽና አንቺን በክብር በምስጋና እናገንሻለን» በማለት እንዳመሰገናት፡፡
ሰአሊተ ምሕረት፡- ሰዓሊተ ምሕረት ማለት ምሕረትን የምትለምን ማለት ነው፡፡ በቅዱስ ገብርኤል ምስክርነት እንደምናገኘው ድንግል ማርያም በእግዚአብሔር ፊት ሞገስን ያገኘች እመቤት ናትና ልመናዋ /ምልጃ ጸሎቷ/ ይሰማል የእናት ልመና አንገት አያስቀልስ ፊት አያስመልስ ነውና፡፡ ሉቃ.1-30፡፡
በእግዚአብሔር ፊት ሞገስ ያገኙ ቅዱሳን ምሕረት ቸርነትን ለምነው አግኝተዋል፡፡ ዘፍ.18-3፣ 23-32፡፡ እግዚአብሔር ሙሴን በፊቴ ሞገስን ስላገኘህ በስምህ ስላወቅሁህ ስለ ሕዝቡ የለመንኸኝን ሁሉ አደርጋለሁ ብሎታል፡፡ ዘጸ.33-12-20፡፡ «ስለ ሙሴ ቃልም ዘወትር ለሕዝቡ ይራራላቸው ነበር» ዘጸ.32-11-14፡፡ ሙሴ በእግዚአብሔር ፊት ሞገስ በማግኘቱ በለመነ ጊዜ እግዚአብሔር እንደ ቃልህ ይቅር አልሁ ይለው ነበር፡፡ ዘኁ.14-20፡፡
በመልአከ ብሥራት በቅዱስ ገብርኤል «በእግዚአብሔር ፊት ሞገስ አግኝተሻል» ተብሎ የተመሰከረላት ድንግል ማርያም የተሰጣት ሞገስ እንደ እናትነቷ ከሁሉ የበለጠ በመሆኑ አጠያያቂ አይደለምና ሰአሊተ ምሕረት እንላታለን፡፡ ማርያም ንጽሕት ድንግል ወላዲተ አምላክ ዠማዕምንት ሰአሊተምህረት ለውሉደ ሰብእ፡- ንጽሕት ድንግል ማርያም የታመነች አምላክን የወለደች ናት ለሰዎች ልጆችም የምሕረት አማላጅ ናት» /ውዳሴ ማርያም ዘዓርብ አንቀጽ 6/
እመቤታችን፡- እመቤት ማለት በአንድ ቤተሰብ መካከል አስተዳዳሪና ሓላፊ የሆነች ታላቅ ሴት ማለት ነው፡፡ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን «ማርያም» የሚለውን በምሥጢራዊ ዘይቤ ሲተረጉሙ እግዝእተ ብዙኃን /የብዙኀን እመቤት/ ብለው ተርጉመውልናል፡፡
በአዳምና በሄዋን አማካኝነት ወደ ዓለም የገባውን መርገም የሻረ ጌታ እግዚአብሔር ከእርስዋ በመወለዱ እምቤታችን /የብዙዎች እመቤት/ ትባላለች፡፡ ሮሜ.5-6-11፡፡ እንዲሁም ዓለም ሁሉ በዳነበት በክርስቶስ የማዳን ሥራ ያመን ክርስቲያኖች ሁሉ በክርስቶስ አንድ ቤተሰብ በመሆናችን ቅድስት እናቱ ድንግል ማርያም እመቤታችን ናት፡፡ ዮሐ.19-26፡፡ ልጇ ጌታችን ነውና እርሷም እመቤታችን ናት፡፡ ሉቃ.1-43፡፡
ቤዛዊተ ዓለም፡- የዓለም መድኃኒት ማለት ነው ድንግል ማርያም የዓለም መድኃኒት ኢየሱስ ክርስቶስን ያስገኘችልን በመሆኗ ቤዛዊተ ዓለም እንላታለን በልጇ ቤዛነት ድነናልና፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለቤዛ ዓለም /ለድኅነተ ዓለም/ በቀራንዮ ኮረብታ የቆረሰው ሥጋ ያፈሰሰው ደም ከድንግል ማርያም የነሣው በመሆኑ ቤዛዊተ ዓለም ትባላለች፡፡ ዕብ.9-22፡፡
የሕያዋን ሁሉ እናት ድንግል ማርያም ለሔዋን ካሣዋ እንደሆነች ሁሉ ለአንስተ ዓለም ሁሉ ካሣ ቤዛ ናት ስድበ አንስትን ወቀሳ ከሰሳ አንስትን አስቀርታለችና፡፡ እንዲሁም ለዓለሙ ሁሉ የምታማልድ በልመናዋ ፍጥረትን የምታስምርና መንግሥተ ሰማያት መርታ የምታስገባ በመሆኗ ቤዛዊተ ዓለም እንላታለን፡፡
ወላዲተ አምላክ፡- ወላዲተ አምላክ ማለት አምላክን የወለደች ማለት ነው፡፡ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል «ከአንቺ የሚወለደው ቅዱሱ የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል፡፡» በማለት የጌታችንን አምላክ ወልደ አምላክነት የድንግል ማርያምን እመ አምላክ ወላዲተ አምላክነት አስረድቶአል፡፡ ሉቃ.1-35 ቅድስት አልሳቤጥም «የጌታዬ እናት ወደ እኔ ትመጣ ዘንድ እንዴት ይሆንልኛል?» ሉቃ.1-44 በማለት እንዳስረዳችው ድንግል ማርያም ጌታችንን የወለደች የጌታችን እናት ናትና ወላዲተ አምላክ እንላታለን፡፡ ድንግል ማርያም «ወላዲተ አምላክ» «አምላክን የወለደች» ተብላእንድትጠራ ለመጀመሪያ ጊዜ በ431 ዓ.ም በኤፌሶን ከተማ በ200 ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን አማካኝነት ተዘጋጅቶ በቅዱስ ቄርሎስ አፈ ጉባኤነት የተመራው 3ኛው ዓለም አቀፋዊ የቤተ ክርስቲያን ሲኖዶስ ነው፡፡ በዚህ ጉባኤ የቀረበው የንስጥሮስ የክህደት ትምህርት «ድንግል ማርያም ወላዲተ አምላክ ልትባል አይገባትም» የሚል ሲሆን ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ንስጥሮሳዊውን ትምህርት አውግዘው ድንግል ማርያም ቅድመ ዓለም የነበረውን አምላክ ለዘመን በሥጋ ስለወለደችው በእውነት አምላክን የወለደች /ወላዲተ አምላክ/ ናት በማለት ትምህርተ ሐዋርያትን አጽንተዋል፡፡
በቤተ ልሔም በከብቶች ግርግም ከድንግል የተወለደው የዓለም ፈጣሪ እግዚአብሔር ነው፡፡ ስለዚህ ድንግል ማርያም ፣ እመ እግዚአብሔር ፣ ወላዲተ አምላክ ተብላ ትጠራለች፡፡ 1ዮሐ.5-20፤ ቲቶ.2-13፡፡
ኪዳነ ምሕረት፡- የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር መዓቱን በምህረት ቁጣውን በትዕግሥት በመመለስ የሰውን ሕይወት ለዘለዓለሙ ለመጠበቅ በመጀመሪያ ከስህተቱ በንስሐ ከተመለሰው ከአዳም፣ ቀጥሎም ከጻድቁ ከኖኅ፣ ከዚያም በእምነትና በምግባሩ ቀናነት የእግዚአብሔር ወዳጅ ተብሎ ከተሰየመው ከአብርሃም.... ከሌሎችም ቅዱሳን ጋር ለመላው የሰው ዘር የሚሆን የምህረትና የበረከት ቃል ኪዳን ገብቷል፡፡
«ከመረጥሁት ጋር ቃል ኪዳኔን አደረግሁ» መዝ.88-3 በማለት በተናገረው መሠረት ከምርጦቹ ጋር ቃል ኪዳን የሚያደርግ ልዑል አምላክ ከተመረጡ የተመጠረች በመሆኗ /ዋ/ ከእናቱ ከቅድስት ድንግል ማርያም ጋር የካቲት 16 ቀን ቃል ኪዳን ሰጥቷታልና ወር በገባ በ16 ቀን ወርኃዊ በዓሏን እናከብራለን፡፡
ይህንንም ለማመልከት ኪዳነ ምሕረት /የምሕረት ቃል ኪዳን የተቀበለች/ ትባላለች፡፡ በዚህም ምክንያት፡-
በእንተ ማርያም መሐረነ ክርስቶስ
ቅድስት ሆይ ለምኝልን
በእንተ ስማ ለማርያም ወዘተ
በማለት የተሰጣትን ቃል ኪዳን መማጸኛ በማድረግ እንጠራታለን፡፡ ምሳሌዋ የሆነች ሐመረ ኖኅ /የኖኅ መርከብ/ በተሰጣት ቃል ኪዳን ከማየ አይኅ /ከጥፋት ውኃ/ ነፍሳትን እንደ አዳነች ቅድስት ድንግል ማርያምም በተሰጣት ቃል ኪዳን ከመከራ ሥጋ ከመከራ ነፍስ ታድነናለችና ኪዳነ ምሕረት /የምሕረት ቃል ኪዳን/ የተሰጠሽ እንላታለን፡፡
ቅድስተ ቅዱሳን፡- ይህ ስም ከፍጡራን በላይ ከፈጣሪ በታች ለሆነች ቅድስት ድንግል ማርያም ንጽሕናና ቅድስና መገለጫ ሆኖ የተሰጣት ልዩ ስም ነው፡፡ ቅድስተ ቅዱሳን ማለት ከተለዩ የተለየች ከተመረጡ የተመረጠች፣ ከተከበሩ የተከበረች ማለት ነው፡፡ ሊቁ ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ ድንግል ማርያምን ባመሰገነበት ክፍል ተሰመይኪ ፍቅርተ ኦ ቡርክት እምአንስት አንቲ ውእቱ ዳግሚት ቀመር እንተ ትሰመይ ቅድስተ ቅዱሳን፡- ከሴቶች ሁሉ ተለይተሽ የተባረክሽ ሆይ የተወደድሽ ተባልሽ ከተለዩ የተለየሽ» በማለት ቅድስናዋን መስክሯል /የእሑድ ውዳሴ ማርያም አንቀጽ 1/
ከአንስተ ዓለም ተለይተው ቅድስናን ገንዘብ ያደረጉ በርካታ ሴቶች ቢኖሩም ድንግል ማርያም ግን የነዚህ ሁሉ ፊት አውራሪ /ግንባር ቀደም/ እና ከሌሎች አንስት የተለየች ቅድስት /ቅድስተ ቅዱሳን/ ትባላለች፡፡ «አንቺ ከሴቶች ሁሉ ተለይተሽ የተባረክሽ ነሽ» በማለት መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል መስክሮላታል፡፡ ሉቃ.1-28፡፡ ከዚህም ጋር በተግባረ ቃል ቅዱስ ኤፍሬም በውዳሴው «የዐቢ ክብራ ለማርያም እምኲሎሙ ቅዱሳን፡- ከቅዱሳን ክብር የማርያም ክብር ይበልጣል» / ዘረቡዕ ውዳሴ ማርያም አንቀጽ .7/ በማለት የድንግል ማርያምን ቅድስና መስክሯል፤ ከዚህም የተነሳ በከበረ ስሟ ቅድስተ ቅዱሳን እያልን እንጠራታለን፡፡
ንጽሕተ ንጹሐን፡- ነጽሐ ነጻ ካለው ግሥ የወጣ ሲሆን ንጽሕት ማለትም የነጻች የጠራች ማለት ነው፡፡ ቅዱሳት መጻሕፍት ስለ ንጽሕና «ዘንጹሕ ልቡ ወንጹሕ እደዊሁ፡- እጆቹም ልቡም ንጹሕ የሆነ»፣ «ብፁዓን ንጹሓነ ልብ ወይለብሱ ንጹሐ፡- ልበ ንጹሖች ብፁዓን ናቸው ንጽሕናን ይለብሳሉ»፣ «ሕያዋት ወንጹሓት፡- ሕያዋንና ንጹሓን»፣ «ንጽሕት ወብርህት፡- የነጻች የምታበራ» በማለት የንጽሕናን ሁኔታ ያስረዳሉ፡፡ መዝ.23፣ ማቴ.5-8፣ ራእ.15፣ ዘሌ.14-4፡፡ ውዳሴ ማርያም ዘአርብ፡፡
በዚህ ዓለም ከሚኖሩ ሴቶች የልማደ አንስት ኃጢአት ሰውነታቸውን ያላጐደፋቸው ወይም ያላረከሳቸው ብዙዎች ናቸው፡፡ ይሁንና ከገቢረ ኃጢአት ንጹሓን ይሁኑ እንጂ ከነቢብና ከሐልዮ ኃጢአት /በመናገርና በማሰብ ከሚሠራ ኃጢአት/ አልነጹም፡፡ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ግን ከገቢር ከነቢብ ከሐልዮ ኃጢአት ንጽሕት ስለሆነች ንጽሕተ ንጹሐን እንላታለን፡፡
ወትረ ድንግል /ዘላለማዊት ድንግል/፡- ቅድስተ ቅዱሳን ወላዲተ አምላክ ማርያም ጌታን ከመጽነሷ በፊት፤ ጌታን በጸነሰች ጊዜ፤ ከጸነሰችም በኋላ፤ ከመውለዷ በፊት፤ በወለደች ጊዜ፣ ከወለደች በኋላ ድንግል ናት ከዚህም የተነሳ ድንግል ዘላለም እንላታለን፡፡ ክህነትን ከነቢይነት ጋር አስተባብሮ የያዘው ሕዝቅኤል ዘላለማዊ ድንግልናዋን መስክሯል፡፡ ሕዝ.44-1-2፡፡
ወትረ ድንግል /ዘላለማዊት ድንግል/፡- ቅድስተ ቅዱሳን ወላዲተ አምላክ ማርያም ጌታን ከመጽነሷ በፊት፤ ጌታን በጸነሰች ጊዜ፤ ከጸነሰችም በኋላ፤ ከመውለዷ በፊት፤ በወለደች ጊዜ፣ ከወለደች በኋላ ድንግል ናት ከዚህም የተነሳ ድንግል ዘላለም እንላታለን፡፡ ክህነትን ከነቢይነት ጋር አስተባብሮ የያዘው ሕዝቅኤል ዘላለማዊ ድንግልናዋን መስክሯል፡፡ ሕዝ.44-1-2፡፡
የአንጾኪያው ሊቀ ጳጳስ ቅዱስ ሳዊሮስ ስለ ቅድስት ድንግል ማርያም ዘላለማዊ ድንግልና በተናገረበት ክፍል «አምላክን የወለደች ማርያም ለዘለዓለሙ ድንግል እንደሆነች መውለዷም የማይመረመር ድንቅ እንደሆነ ከወለደችም በኋላ በድንግልና ጸንታ እንደኖረች አስረዳን» በማለት ስለ ዘላለማዊ ድንግልናዋ መስክሯል፡፡ ኢሳ.7.14፤ ሉቃ.1.27፡፡
ድንግል በክልኤ፡- በሁለት ወገን ድንግል ማለት ነው፡፡ በሁለት ወገን በሥጋም በነፍስም በሐልዮ /በሐሳብ/ በገቢር /በመሥራት/ በውስጥ በአፍአ ድንግል መሆኗን ያመለክተናል፡፡
ሌሎች ሰዎች ከገቢር ከነቢብ ቢጠበቁ ከሐልዮ /ከሃሳብ/ ኃጢአት መጠበቅ ግን አይቻላቸውም፡፡ ድንግል ማርያም ግን በሁለት ወገን ንጽሕት ቅድስት ናት ስለዚህ ድንግል በክልኤ /በሁለት ወገን ድንግል/ ትባላለች፡፡
ድንግል ወእም፡- እናትም ድንግልም ማለት ነው፡፡ እናትነትን ከድንግልና ጋር አስተባብሮ መገኘት ለፍጥረታዊ ሰው የማይቻል ቢሆንም ድንግል ማርያም ግን ሁለቱንም አስተባብራ ይዛለችና ድንግል ወእም ትባላለች፡፡
ሴቶች በልጅ ጸጋ ከከበሩ ድንግልናቸውን ያጣሉ በድንግልና ተወስነው ጸጋ እግዚአብሔርን ለማግኘት ከወሰኑ ደግሞ ከልጅ ጸጋ ይለያሉ፡፡ ሁለቱንም አስተባብረው ይዘው መገኘት አይሆንላቸውም፡፡ ድንግል ማርያም ግን ድንግልናን ከእናትነት እናትንትን ከድንግልና ጋር አስተባብራ ይዛ የተገኘች በመሆንዋ ድንግል ወእም እናትም ድንግልም ሆናለች፡፡ ሉቃ.1-26-38፡፡
ልጇ ክርስቶስም አምላክ ወሰብእ /ፍጹም አምላክ ፍጹም ሰው/ ሲባል እንዲኖር እርሷም ድንግል ወእም ስትባል ትኖራለች ስትወልደው ማኅተመ ድነግልናዋ እንዳልተለወጠ ሁሉ ባሕርየ መለኮቱ አልተለወጠም «እኔ እግዚአብሔር አልለወጥም» እንዳለ፡፡ ሚል.3-6፡፡
ከላይ የተጠቀሱት ሁሉም ምሥጢራዊና ትርጉም ያላቸው የእመቤታችን ስሞች የተገለጹት /የተነገሩት/ በራሱ በልዑል እግዚአብሔር እንዲሁም በቅዱሳን ነቢያት፣ በቅዱሳን ሐዋርያት፣ በቅዱሳን ጻድቃን ሰማዕታትና በሌሎችም ቅዱሳን አባቶች ነው፡፡
ይህም ምሥጢር የትምህርተ ሃይማኖት አንዱ አካል ሲሆን እኛም በቅዱሳን የተገለጸውን የእመቤታችንን ምሥጢራዊና ትርጉም ያላቸው ስሞች ተረድተን የትምህርተ ሃይማኖት ዕውቀታችንን ልናሳድግ ቅድስት ድንግል ማርያምንም ልናከብር እንዲገባን መገንዘብ አለብን፡፡ የቅዱሳንም አስተምህሮት ይህ ነውና፡፡
ስም አጠራሯ የከበረ ቅድስተ ቅዱሳን፣ እመ ብርሃን፣ ሰአሊተ ምሕረት፣ ድንግል ወእም፣ ወላዲተ አምላክ፣ እየተባለች የምትጠራ ድንግል ማርያም ረድኤትና በረከቷ አማላጅነቷ አይለየን፡፡ አሜን፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔ
ስብከት
ቅድስት ቤተክርስቲያን አምልኮቷን የምትፈጽምበት እጅግ የተደራጀ ሥርዐተ አምልኮ አላት፡፡ ከዚህ ሥርዓተ አምልኮ አንዱ ክፍል ዓመታዊ የምስጋና መርሐ ግብር እና የሥርዓተ ትምህርት ነው፡፡ ይህም በሁለት መልኩ የተደራጀ ነው፡፡
ሀ. ቀናትን መሠረት በማድረግ
በእግዚአብሔርና በሰው ልጆች ግንኙነት ውስጥ ጥልቅ ቦታ የሚሰጣቸው ድርጊቶች እና ክንውኖች በዓመቱ ውስጥ ቀናት ተመድበውላቸው በበዓላትና በአጽዋማት መልክ ይታሰባሉ፡፡ ቅድስት ቤተክርስቲያን እነዚህን በዓላትና አጽዋማት የምታከብርበት ዓመታዊ መርሐ ግብር እና በበዓላቱና በአጽዋማቱ የሚታሰበውን ነገር አስመልክቶ አባላቶችን የምታስተምርበት ሥርዓተ ትምህርት አላት፡፡
እንደዚህ ባለ መርሐ ግብር ከሚታሰቡት መካከል ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዘመነ ሥጋዌው ያደረጋቸው ነገሮችና ያስተማራቸው ትምህርቶች /ፅንሰት፣ ልደት፣ ጥምቀት፣ ስቅለት፣ ትንሳኤ፣ ዕርገት፣ ደብረ ታቦር፣ምጽአት/፤ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም በዓላት /ልደቷ፣ ዕረፍቷ፣ ቤተመቅደስ መግባቷ፣ ድንቅ ተአምራት ያደረገችባቸው ዕለታት/፤፣ የቅዱሳን በዓላት /ልደታቸው፣ ዕረፍታቸው፣ ተአምራት ያደረጉባቸው. . / ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡
እንደዚህ ባለ መርሐ ግብር ከሚታሰቡት መካከል ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዘመነ ሥጋዌው ያደረጋቸው ነገሮችና ያስተማራቸው ትምህርቶች /ፅንሰት፣ ልደት፣ ጥምቀት፣ ስቅለት፣ ትንሳኤ፣ ዕርገት፣ ደብረ ታቦር፣ምጽአት/፤ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም በዓላት /ልደቷ፣ ዕረፍቷ፣ ቤተመቅደስ መግባቷ፣ ድንቅ ተአምራት ያደረገችባቸው ዕለታት/፤፣ የቅዱሳን በዓላት /ልደታቸው፣ ዕረፍታቸው፣ ተአምራት ያደረጉባቸው. . / ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡
ለ. እሁዶችን /ሳምንታትን/ መሠረት በማድረግ
በዓመቱ ውስጥ ያሉት ቀናት/ከመስከረም 1 እስከ ጳጉሜን 5/ ብቻ ሳይሆኑ እሁዶቹም/ሳምንታቱም/ የተለያዩ ነገሮች ይታሰቡባቸዋል፡፡ በዓመቱ ውስጥ ባሉት እሁዶች /ሳምንታት/ በእያንዳንዳቸው የሚቀርበው ምስጋና እና የሚሰጠው ትምህርት ምን እንደሆነ የሚገልጽ መርሐ ግብር እና ሥርዓተ ትምህርት አላት፡፡ ለምሳሌ ከመስከረም 1 እስከ 7 ድረስ ያለው እሁድ /ወይም በዚህ እሁድ የሚጀምረው ሳምንት/ «ዮሐንስ አኅድአ»፣«ዮሐንስ መሰከረ ይባላል፡፡ የቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ ሕይወት እና ምስክርነት የሚታሰብበት ነው፡፡
መስከረም 8 ቀን እሁድ ቀን ቢውል ያ እሁድ «ዘካርያስ» ተብሎ ይጠራና የመጥመቁ ዮሐንስ አባት የካህኑ የዘካርያስ ነገር ይታሰብበታል፡፡
ከመስከረም 9 እስከ 17 ያለው እሁድ /እና በዚህ እሁድ የሚጀምረው ሳምንት/ «ፍሬ» ይባላል፡፡ በዚህ እሁድ እግዚአብሔር ለምድር ፍሬን እንደሚሰጥ ይታሰባል፡፡
በዚህ መልኩ በዓመቱ ውስጥ ባሉት እሑዶች በሙሉ ምን እንደሚታሰብ የሚገልጽ መርሐ ግብርና ሥርዓተ ትምህርት አለ፡፡ ይህም በተለያዩ ወቅቶች ያለውን የአየር ጠባይ እና የግብርና እንቅስቃሴ ያገናዘበ ነው፡፡
መስከረም 8 ቀን እሁድ ቀን ቢውል ያ እሁድ «ዘካርያስ» ተብሎ ይጠራና የመጥመቁ ዮሐንስ አባት የካህኑ የዘካርያስ ነገር ይታሰብበታል፡፡
ከመስከረም 9 እስከ 17 ያለው እሁድ /እና በዚህ እሁድ የሚጀምረው ሳምንት/ «ፍሬ» ይባላል፡፡ በዚህ እሁድ እግዚአብሔር ለምድር ፍሬን እንደሚሰጥ ይታሰባል፡፡
በዚህ መልኩ በዓመቱ ውስጥ ባሉት እሑዶች በሙሉ ምን እንደሚታሰብ የሚገልጽ መርሐ ግብርና ሥርዓተ ትምህርት አለ፡፡ ይህም በተለያዩ ወቅቶች ያለውን የአየር ጠባይ እና የግብርና እንቅስቃሴ ያገናዘበ ነው፡፡
በእነዚህ ዕለታት ምስጋና የሚቀርብበት እና ትምህርት የሚሰጥበትን ጉዳይ /ርእስ/ መወሰን ብቻ ሳይሆን በጉዳዩ ላይ ዝርዝር ነገሮችም ተዘጋጅተዋል፡፡
«ስንክሳር» የሚባለው መጽሐፍ ከመስከረም አንድ እስከ ጳጉሜን 5/6 ድረስ የሚታሰቡ ቅዱሳንን እና ክንውኖችን ዝርዝር ታሪክ ይዟል፡፡
«ግጻዌ» የሚባለው መጽሐፍ በየዕለቱ /በየእሁዱ/ ከሚታሰበው ጉዳይ ጋር ተያያዥነት ያላቸው አምስት የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባባት /ከመልእከታተ ጳዉሎስ፣ ከሰባቱ መልእክታተ ሐዋርያት፣ ከሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ፣ ከመዝሙረ ዳዊት፣ ከወንጌል/ መርጦ ያቀርባል፡፡
የቅዱስ ያሬድ የዜማ መጻሕፍትም /ድጓ፣ ዝማሬ፣ምዕሪፍ፣ ዝማሬ መዋስዕት/ በዚህ መርሐ ግብር መሠረት የተዘጋጁ ሲሆኑ በየዕለቱ ስለሚታሰቡት ነገር ዝርዝር እና ጥልቅ የሆኑ ትምህርቶችን እና ምስጋናዎችን የያዙ ናቸው፡፡
በዚህ «ስብከት» በሚለው ዓምድ ሥር ይህንን መርሐ ግብር፣ ሥርዓተ ትምህርት መሠረት አድርገን ትምህርቶችን እናቀርባለን፡፡ በአጠቃላይ በዚህ ዓምድ ስር የሚቀርቡት ትምህርቶች ሦስት ዓይነት ናቸው፡፡
1. ሳምንታዊ ስብከት- በዚህ ንዑስ ዓምድ ስር በእያንዳንዱ እሁድ/ሳምንት/ የሚታሰቡትን ጉዳዮች አስመልክቶ ትምህርቶች ይቀርባሉ፡፡
2. ወቅታዊ ስብከት- በዚህ ንዑስ ዓምድ ስር ቀናትን መሠረት አድርገው ከሚከበሩት በዓላት መካከል ዋና ዋናዎቹን በተመለከተ ትምህርቶች ይቀርባሉ፡፡
3. ሌሎች- ይህ ንዑስ ዓምድ በተለያዩ ርእሰ ጉዳዮች ላይ የተዘጋጁ ስብከቶች የሚቀርቡበት ነው፡፡
አዘጋጆቹን በጸሎት በማሰብ፣ በሚቀርቡ ስብከቶች ላይ አስተያየት በመስጠትና ስብከቶችን በመላክ ለዚህ ዓምድ መጠናከር ሁላችንም የበኩላችንን አስተዋጽኦ እናድርግ፡፡ እግዚአብሔር ሐሳባችንን እንድንፈጽም ቅዱስ ፈቃዱ ይሁንልን፡፡
«ስንክሳር» የሚባለው መጽሐፍ ከመስከረም አንድ እስከ ጳጉሜን 5/6 ድረስ የሚታሰቡ ቅዱሳንን እና ክንውኖችን ዝርዝር ታሪክ ይዟል፡፡
«ግጻዌ» የሚባለው መጽሐፍ በየዕለቱ /በየእሁዱ/ ከሚታሰበው ጉዳይ ጋር ተያያዥነት ያላቸው አምስት የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባባት /ከመልእከታተ ጳዉሎስ፣ ከሰባቱ መልእክታተ ሐዋርያት፣ ከሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ፣ ከመዝሙረ ዳዊት፣ ከወንጌል/ መርጦ ያቀርባል፡፡
የቅዱስ ያሬድ የዜማ መጻሕፍትም /ድጓ፣ ዝማሬ፣ምዕሪፍ፣ ዝማሬ መዋስዕት/ በዚህ መርሐ ግብር መሠረት የተዘጋጁ ሲሆኑ በየዕለቱ ስለሚታሰቡት ነገር ዝርዝር እና ጥልቅ የሆኑ ትምህርቶችን እና ምስጋናዎችን የያዙ ናቸው፡፡
በዚህ «ስብከት» በሚለው ዓምድ ሥር ይህንን መርሐ ግብር፣ ሥርዓተ ትምህርት መሠረት አድርገን ትምህርቶችን እናቀርባለን፡፡ በአጠቃላይ በዚህ ዓምድ ስር የሚቀርቡት ትምህርቶች ሦስት ዓይነት ናቸው፡፡
1. ሳምንታዊ ስብከት- በዚህ ንዑስ ዓምድ ስር በእያንዳንዱ እሁድ/ሳምንት/ የሚታሰቡትን ጉዳዮች አስመልክቶ ትምህርቶች ይቀርባሉ፡፡
2. ወቅታዊ ስብከት- በዚህ ንዑስ ዓምድ ስር ቀናትን መሠረት አድርገው ከሚከበሩት በዓላት መካከል ዋና ዋናዎቹን በተመለከተ ትምህርቶች ይቀርባሉ፡፡
3. ሌሎች- ይህ ንዑስ ዓምድ በተለያዩ ርእሰ ጉዳዮች ላይ የተዘጋጁ ስብከቶች የሚቀርቡበት ነው፡፡
አዘጋጆቹን በጸሎት በማሰብ፣ በሚቀርቡ ስብከቶች ላይ አስተያየት በመስጠትና ስብከቶችን በመላክ ለዚህ ዓምድ መጠናከር ሁላችንም የበኩላችንን አስተዋጽኦ እናድርግ፡፡ እግዚአብሔር ሐሳባችንን እንድንፈጽም ቅዱስ ፈቃዱ ይሁንልን፡፡
ክርስትና በእምነት እያደጉ እና እየጠነከሩ ዘወትር የሚጎለብቱበት ሕይወት ነው፡፡ በመሆኑምአንድ ክርስቲያን ከትናንት ዛሬ ከአምና ዘንድሮ አድጎና ጠንክሮ መገኘት አለበት፡፡ «ንቁ በሃይማኖት ቁሙ ጎልምሱ ጠንክሩ» እንደተባለ በጊዜውም /በተመቸ ጊዜ/ ያለጊዜውም/ባልተመቸ ጊዜም/ በእምነት ጸንቶ ለመገኘትና እስከ ሞት ድረስ ለመታመን የግድ በእምነት አድጎና ጠንክሮ መገኘት ያስፈልጋል፡፡ /1ቆሮ.6.13ጠ14/፡፡ እምነትን በምግባርና በትሩፋት ለመግለጽም ራስን በመካድ ፈቃደ ሥጋን ለፈቃደ ነፍስ ማስገዛት ይገባል፡፡ ለዚህም መከራን እየታገሱ ራስን ከዓለም መለየት ይገባል፡፡ በዚህ ዓይነት ፈቃደ ሥጋውን ለፈቃደ ነፍሱ በማስገዛት በእምነቱ የጠነከረ ሰው ከማናቸውም ነገር ይልቅ መንግሥቱንና ጽድቁን ያስቀድማል፡፡ /ማቴ.6.13/፡፡ ይህም ማለት ሃይማኖትን ከምግባር አዋሕዶ ልጅነቱን አጽንቶ ጽድቅ የሚገኝበትን ሀገር መንግሥተ ሰማያትን ተስፋ አድርጎ ይኖራል ማለት ነው፡፡ በዚህም የመንፈስን ፍሬ የሚያፈራ በአፀደ ቤተ ክርስቲያን የተተከለ የሃይማኖት ተክል ይሆናል፡፡ /ገላ.5.22/፡፡ ተክልነቱም በውኃ ፈሳሾች ዳር እንደተተከለች ፍሬዋን በየጊዜው እንደምትሰጥ፣ ቅጠልዋም እንደማይረግፍ ዛፍ ነው፡፡ እንዲህ ዓይነቱም ሰው በክፋዎች ምክር አይሄድም፡፡ በኃጢአተኞችም መንገድ አይቆምም፡፡ በዋዘኞችም ወንበር አይቀመጥም፤ ነገር ግን በእግዚአብሔር ሕግ ደስ ይለዋል፡፡ ሕጉንም በቀንና በሌሊት ያስባል፡፡ /መዝ.1.3/፡፡
ቅዱስ ጳዉሎስ የተሰሎንቄ ምእመናን በእምነት አድገውና ጠንክረው በማየቱ «በጸሎታችን ጊዜ ስለ እናንተ ስናስብ የእምነታችሁን ሥራ የፍቅራችሁንም ድካም በጌታችንም በኢየሱስ ክርስቶስ ያለውን የተስፋችሁን መጽናት በአምላካችንና በአባታችን ፊት ሳናቋርጥ እያሰብን እግዚአብሔርን ሁልጊዜ በሁላችሁ ምክንያት እናመሰግናለን፡፡» በማለት ስለእነርሱ እግዚአብሔርን አመስግኗል፡፡ /1ተሰ.1.2ጠ3/፡፡ ከጥንት ጀምሮ በእምነታቸው ጠንካሮች የነበሩ ሰዎች በጉዟቸው ሁሉ እግዚአብሔርን ደስ አሰኝተዋል፡፡ እግዚአብሔርም ደስ የተሰኘባቸው በእምነታቸው ጸንተው በጎ ሥራ በመሥራታቸውና ዓለምን ድል በማድረጋቸው ነው፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳዉሎስ በዕብራውያን መልእክቱ እንደዘረዘረው፡
• አቤል ከቃየል ይልቅ የሚበልጥ መሥዋዕትን ያቀረበው፣
• አብርሃም ከዘመዶቹ ተለይቶ ከሀገሩ የወጣው፤ አንድ ልጁን ይስሐቅንም ለመሠዋት ፈቀደኛ የሆነው፣
• ሙሴ የግብጽን ብዙ ገንዘብ የናቀውና ከወገኖቹ ጋር መከራ መቀበልን የመረጠው፤ የፈርኦን የልጅ ልጅ እንዳይባል እምቢ ያለው፣
• ሙሴ የግብጽን ብዙ ገንዘብ የናቀውና ከወገኖቹ ጋር መከራ መቀበልን የመረጠው፤ የፈርኦን የልጅ ልጅ እንዳይባል እምቢ ያለው፣
የኢያሪኮ ግንብ በእስራኤላውያን ጩኸት የፈረሰው፣
• ጌዴዎንና ባርቅ፣ሶምሶንና ዮፍታሔ ጠላቶቻቸውን ድል ያደረጉት፣
• ብላቴናው ዳዊት ኃይለኛውን ጎልያድን ያሸነፈው፣
• ሠለስቱ ደቂቅ ወደ እቶነ እሳት ቢጣሉም ከመቃጠል የዳኑት በእምነት ነው፡፡ /ዕብ.11.1ጠ4/፡፡
በአዲስ ኪዳንም ቅዱሳን ሐዋርያት ሁሉን ትተው እስከ መጨረሻው የተከተሉት በእምነት ነው፡፡ /ማቴ.19.27/ ከእነርሱም ሌላ በሰው ዘንድ ያልተጠበቁ፣ በእርሱ ዘንድ ግን የታወቁ ጥቂት ሰዎች የእምነታቸው ጽኑነት ተመስክሮላቸዋል፡፡ ለምሳሌ ከነናዊቷ ሴት «አንቺ ሴት እምነትሽ ታላቅ ነው እንደ ወደድሽ ይሁንልሽ» ተብላለች፡፡ /ማቴ. 15.28/፡፡ በእምነት የጸኑ ሰዎች የቤተክርስቲያንን ሥርዓት፣ ትውፊት ለመጠበቅ መልካሙን ገድል ይጋደላሉ፡፡ /2ጢሞ.4.7/፡፡
አንድ ክርስቲያን በክርስትና ሕይወት እስከ ሞት ድረስ ታምኖ የመንግሥቱ ወራሽ ለመሆን ሊያከናውናቸው ከሚገቡ መንፈሳዊ ተግባራት ጥቂቶችን እንመለከታለን፡፡
አንድ ክርስቲያን በክርስትና ሕይወት እስከ ሞት ድረስ ታምኖ የመንግሥቱ ወራሽ ለመሆን ሊያከናውናቸው ከሚገቡ መንፈሳዊ ተግባራት ጥቂቶችን እንመለከታለን፡፡
1. የእግዚአብሔር ስጦታዎች ሁሉ ለበጎ መሆናቸውን ማመን
በማናቸውም ጊዜ እግዚአብሔር ሁሉን የሚሰጥ አምላከ መሆኑን መዘንጋት የለብንም፡፡ ሌላው ቀርቶ ለእኛ ክፉ የሚመስሉን ነገሮችን እንኳን ለበጎ መሆናቸው ማመን አለብን፡፡ /ሮሜ.8.28/፡፡ ምክንያቱም እግዚአብሔር ክፉውን ወደ በጎ ሊለውጥ የሚችል ኃያል አምላክ ነውና፡፡ ብላቴናው ዮሴፍ ባሪያ አድርገው የሸጡትን ወንድሞቹን «እናንተ ክፉ ነገር አሰባችሁብኝ እግዚአብሔር ግን ዛሬ እንደ ሆነው ብዙ ሕዝብ እንዲድን ለማድረግ ለመልካም አሰበው፡፡» ያላቸው ለዚህ ነው፡፡ /ዘፍ.50.20/፡፡ አበ ብዙኃን አብርሃም እግዚአብሔር «ልጅህን ሠዋልኝ» ያለው ለበጎ እንደሆነ ያውቅ ነበር፡፡ ማወቅም ብቻ ሳይሆን እንደተባለው ልጁን ቢሠዋ እንኳን ከሞት አስነሥቶ በእርሱ በኩል ዘሩን እንደሚያበዛለት ያምን ነበር፡፡ /ዕብ.11.17/፡፡ ኢዮብም ነገር ሁሉ ለበጎ እንደሆነ አውቆ «እግዚአብሔር ሰጠ እግዚአብሔርም ነሣ የእግዚአብሔር ስም የተባረከ ይሁን» ብሏል፡፡ /ኢዮ.1.21/፡፡
2. የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳኖች ማመን
2. የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳኖች ማመን
ብዙ ሰዎች እግዚአብሔር የሰጣቸው ተስፋ ደርሶ ቃሉ የሚፈፀም አይመስላቸውም፡፡ ነገር ግን የእግዚአብሔር ቃል ያለጥርጥር ይፈጸማል፡፡ ለአዳምና ለሔዋን የተሰጠው ተስፋ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ቤዛነት ተፈጽሟል፡፡ /ዘፍ.3.15/፡፡ ለኤልያስ የተሰጠው ተስፋ ምንድን ነው) የተሰጠው ተስፋ በሰራፕታዊቷ ሴት መጋቢነት ሲፈጸም ታይቷል፡፡ እንዲሁም በነቢዩ በኢዩኤል አንደበት የተነገረው ተስፋ የበዓለ ሃምሣ ዕለት ለቅዱሳን ሐዋርያት በመሰጠቱ ተፈጽሟል፡፡ /ኢዩ.2.28፤ ሐዋ.2.16/፡፡ በዚህ ዓይነት እግዚአብሔር ለሕዝቡ የገባውን ቃል ኪዳን እንደማይሽርና ከአፉ የወጣውን ቃል እንደማይለውጥ ማመን ይገባል፡፡/መዝ.88.34/፡፡ በቤተ ክርስቲያን በምንሰበሰብበት ጊዜ ሁለት ወይም ሦስት በስሜ በሚሰበሰቡት በዚያ እኔ በመካከላቸው እሆናለሁ ባለው መሠረት በመካከላችን እንደሚገኝ የታመነ ነው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ቤተ ክርስቲያን ከውስጥም ሆነ ከውጭ መከራ በሚበዛባት ጊዜ መከራ የሚያስነሣባትና የሚያጸናባት ዲያብሎስ መሆኑን አውቀን «የገሃነም ደጆችም አይችሉአትም» በሚለው ቃል ኪዳን መጽናት ይገባል፡፡ /ማቴ.16.18/፡፡ መናፍቃን ከእውነት መንገድ ለማውጣት በሚከራከሩን ጊዜም «ወደረኞቻችሁ ሁሉ ሊቃወሙና ሊከራከሩ የማይችሉትን አፍና ጥበብ እሰጣችኋለሁ»የሚለውን ቃል ኪዳን በማሰብ መታመን ያስፈልጋል /ሉቃ.21.15/፡፡
3. በችግር ጊዜ የእግዚአብሔርን ቸርነትና ፈቃድ ተስፋ ማድረግ
በመንፈሳዊ ጎዳና ስንጓዝ በየአቅጣጫው የሚከበንን መከራ አይተን ተስፋ መቁረጥ ሳይሆን ወደ እግዚአብሔር ተመልክተን አዳኝነቱን ተስፋ ማድረግ አለብን፡፡ ሊቀ ነቢያት ሙሴ ወገኖቹ እስራኤል ቀይ ባሕርን ከኋላ ደግሞ የፈርኦንን ሠራዊት ተመልክተው ተስፋ በቆረጡ ጊዜ «ቁሙ፣ ዛሬ ለእናንተ የሚያደርጋትን የእግዚአብሔርን ማዳን እዩ፡፡» ያላቸው ለዚህ ነው፡፡ /ዘዳ.14.13ጠ14/፡፡
ብላቴናው ዳዊት የተመለከተው በአካሉ ግዙፍ ወደሆነው ወደ ጎልያድ ሳይሆን ወደ እግዚአብሔር አዳኝነት ነው፡፡ /1ሳሙ.17.46/፡፡በአጠቃላይ ዓለም ድብልቅልቅ ቢል ተስፋመቁረጥ አይገባም፡፡ ምክንያቱም «እግዚአብሔር በወጀብና በዓውሎ ነፋስ መካከል መንገድ አለውና»/ናሆ.1.3/፡፡
ብላቴናው ዳዊት የተመለከተው በአካሉ ግዙፍ ወደሆነው ወደ ጎልያድ ሳይሆን ወደ እግዚአብሔር አዳኝነት ነው፡፡ /1ሳሙ.17.46/፡፡በአጠቃላይ ዓለም ድብልቅልቅ ቢል ተስፋመቁረጥ አይገባም፡፡ ምክንያቱም «እግዚአብሔር በወጀብና በዓውሎ ነፋስ መካከል መንገድ አለውና»/ናሆ.1.3/፡፡
4. የቅዱሳንን ገድል ማሰብ
ቅዱሳን አንድ ጊዜ ስለተሰጣቸው ሃይማኖት እሰከ መጨረሻው ተጋድለዋል፡፡ /2ጢሞ.4.7/፡፡ በሰይፍ ተመትተዋል፣ በእሳት ተቃጥለዋል፣ ለአናብስት ተሰጥተዋል፣ ወደ ጥልቅ ባሕር ተጥለዋል፣ ይህም የሚያሳየን የእምነታቸውን ጥንካሬ ነው፡፡ በመሆኑም የቅዱሳንን ገድል በምናስብበት ጊዜ ከእነርሱ የምንማረው እምነታቸውን፣ ሥርዓታቸውንና ትውፊታቸውን ለመጠበቅ መጽናታቸውን ነው፡፡ መማርም ብቻ ሳይሆን በተሰጣቸው ቃል ኪዳንም እንጠቀማለን፡፡ እስራኤል ዘሥጋ «እናንተ ጽድቅን የምተከተሉ እግዚአብሔርንም የምትሹ ስሙኝጠ ከእርሱ የተቆረጣችሁበትን ድንጋይ ከእርሱም የተቆፈራችሁበትን ጉድጓድ ተመልከቱ፣ ወደ አባታችሁ ወደ አብርሃም ወደ ወለደቻችሁም ወደ ሣራ ተመልከቱ፡፡ አንድ ብቻውን በሆነ ጊዜ ጠራሁት፣ ባረኩትም፣ አበዛሁትም፡፡» የተባለለት ለዚህ ነው፡፡ /ኢሳ.51.1/፡፡
ቅዱስ ጳውሎስም «የእግዚአብሔርን ቃል የተናገሩአችሁን ዋኖቻችሁን አስቡ የኑሮአቸውንም ፍሬ እየተመለከታችሁ በእምነታቸው ምሰሉአቸው» ብሏል /ዕብ.13.7/፡፡ በአጠቃላይ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር መሆኑንና ሥራችንን ሁሉ እንደሚከናውንልን፣ ከሁሉም በላይ እንደሚወደን ማመን ያስፈልጋል፡፡ /ዘፍ.15.21፤1.22፤ መሳ.16.3/፡፡ ምክንያቱም አንድ ልጁን እንኳን አልከለከለንምና /ዮሐ.3.16/፡፡ የእግዚአብሔር ፍቅር በእኛ ዘንድ ተገለጠ፣ በእርሱም በኩል በሕይወት እንኖር ዘንድ እግዚአብሔር አንድ ልጁን ወደ ዓለም ልኮታልና፡፡ /1ዮሐ.4.9/፡፡ እርሱም በትምህርቱ «ከእንግዲሀ ወዲህ ባሮች አልላችሁም ወደጆች ግን ብያችኋለሁ» ብሎናልና፡፡ /ዮሐ.15.15/፡፡ በመጨረሻም ስለማናቸውም ነገር እንደምንጸልይ ሁሉ ስለ እምነታችንም ጽናት ልንጸልይ ይገባል፡፡ እንዲህ ከሆነ እምነታችን ዕለት ዕለት እያደገ እየጠነከረ ይሄዳል፡፡ በአንጻሩ ደግሞ እስከ ሞት ድረስ እንዳንታመን በእምነትና በምግባር እንዳንጸና የሚያደርጉን ፈተናዎች አሉ፡፡ ከእነዚህም ውስጥ ጥቂቶቹ፡
ቅዱስ ጳውሎስም «የእግዚአብሔርን ቃል የተናገሩአችሁን ዋኖቻችሁን አስቡ የኑሮአቸውንም ፍሬ እየተመለከታችሁ በእምነታቸው ምሰሉአቸው» ብሏል /ዕብ.13.7/፡፡ በአጠቃላይ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር መሆኑንና ሥራችንን ሁሉ እንደሚከናውንልን፣ ከሁሉም በላይ እንደሚወደን ማመን ያስፈልጋል፡፡ /ዘፍ.15.21፤1.22፤ መሳ.16.3/፡፡ ምክንያቱም አንድ ልጁን እንኳን አልከለከለንምና /ዮሐ.3.16/፡፡ የእግዚአብሔር ፍቅር በእኛ ዘንድ ተገለጠ፣ በእርሱም በኩል በሕይወት እንኖር ዘንድ እግዚአብሔር አንድ ልጁን ወደ ዓለም ልኮታልና፡፡ /1ዮሐ.4.9/፡፡ እርሱም በትምህርቱ «ከእንግዲሀ ወዲህ ባሮች አልላችሁም ወደጆች ግን ብያችኋለሁ» ብሎናልና፡፡ /ዮሐ.15.15/፡፡ በመጨረሻም ስለማናቸውም ነገር እንደምንጸልይ ሁሉ ስለ እምነታችንም ጽናት ልንጸልይ ይገባል፡፡ እንዲህ ከሆነ እምነታችን ዕለት ዕለት እያደገ እየጠነከረ ይሄዳል፡፡ በአንጻሩ ደግሞ እስከ ሞት ድረስ እንዳንታመን በእምነትና በምግባር እንዳንጸና የሚያደርጉን ፈተናዎች አሉ፡፡ ከእነዚህም ውስጥ ጥቂቶቹ፡
1. የራስን ክብር መሻት
ብዙ ሰዎች የእግዚአብሔርን ክብር ትተው የራሳቸውን ምድራዊ ክብር ሲፈልጉ እምነታቸው ደክሞባቸዋል፡፡ ዲያብሎስ ከክብሩ የተዋረደው፣ ሄሮድስ ሕፃኑን ኢየሱስ ክርስቶስን ለመግደል ያሳደደው፣ ፈሪሳውያን እርስ በርሳቸው ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ «እነሆ ዓለሙ ሁሉ በኋላው ተከትሎት ሄዷል፡፡» በማለት ይቃወሙት የነበረው የራስን ክብር በመሻት ነው፡፡ /ማቴ.2.17፤ ዮሐ.12.19/፡፡ ይሁን እንጂ ምድራዊ ክብር ፈጥኖ እንደ ሣር ይጠወልጋል፣ እንደ አበባም ይረግፋል፡፡ /ኢሳ.40.6፤1ጴጥ.1.24/፡፡ ስለሆነም እንደ ቅዱስ ጳውሎስ «ነፍሴን/ሰውነቴን/ በእኔ ዘንድ እንደማትከብር እንደ ከንቱ ነገር እቆጥራለሁ» ማለት ይገባል፡፡
2. እምነትንና ዕውቀትን መደባለቅ
የሰው ልጅ አእምሮው ውሱን፣ ዕውቀቱም የተገደበ ስለሆነ ነገረ ሃይማኖትን ከአቅሙ በላይ ለመተንተን ይከብደዋል፡፡ ስለሆነም የረቀቀውን የእግዚአብሔርን አሠራር ስፋቱንና ጥልቀቱን በሥጋዊ ዕውቀቱ እመረምራለሁ ሲል ከተሳሳተ ሀሳብ ላይ ደርሶ ይሰናከላል፡፡ በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ላይ እንደምናየው በመጀመሪያው መቶ ክፍለ ዘመን የነበሩት ግኖስቲኮች ከሃይማኖት ተሳስተው የወደቁት፣ ሃይማኖትንና ዕውቀትን በመደባለቅ ለመጓዝ ባደረጉት ሙከራ ነው፡፡ ሥጋዊውን ዓለም ልንመረምር እንችላለን እንጂ የመንፈስ ቅዱስን ሥራ ልንመረምር አንችልም፡፡ በመሆኑም ሊቃውንት በእምነት ተራቅቀው ብዙ የሃይማኖትን ምሥጢር ባወቁ ቁጥር የሚያውቁት ገና አለማወቃቸውን ነው፡፡ ስለሆነም ውሱን የሆነ ዕውቀታችንን በትህትናና በትዕግሥት እግዚአብሔርን ከማገልገል ጋር ልንጠቀምበት ይገባል፡፡
3. ክፉ ባልንጀርነት
ከመናፍቃን ጋር በመወዳጀት የእነርሱን ስብከትና መዝሙር መስማት እምነትን ያደክማል፡፡ ምክንያቱም የመዝሙሩ መሣሪያና ስሜት ለሥጋዊ ሀሳብና ፈቃድ መጥፎ ጎን መነሣሣት ይፈጥራልና፡፡ ሃይማኖታዊ ሳይሆን ስሜታዊ ያደርጋል፡፡ የዜማው ስልተ አልባ መሆንናከዘፈን ጋር ተመሳሳይ በመሆኑ ዓለማዊነት ጠባይ የለበትም መንፈሳዊ ነው ለማለት ያዳግታል፡፡ ለዚህም ነው «ክፉ ባልንጀርነት መልካሙን አመል ያጠፋዋል» የተባለው /1ቆሮ.15.33/፡፡ በሃይማኖት በሥርዓት ከማይመስል ጋር ለመመሳሰል መሞከር፣ አብሮ ማደርም ሆነ መዋል መልካሙን እምነት ያጠፋዋል፡፡ ቅዱስ ዮሐንስም በመልእክቱ «በቤታችሁ አትቀበሉት ሰላምም አትበሉት ሰላምም የሚለው ሰው በክፉ ሥራው ይካፈላልና፡፡» ብሏል፡፡ /2ዮሐ.1.10 - 12/፡፡ ቅዱስ ጳውሎስም «ከማያምን ጋር በማይመች አካሄድ አትጠመዱ፡፡» ብሏል፡፡ ስለሆነም ብርሃን ከጨለማ ጋር ምንም አንድነት ስለሌለው መለየት ያስፈልጋል፡፡ /2ቆሮ. 6.14-16/፡፡
4. ክፉ ወሬ
ምእመናን ስለ ሃይማኖታቸው መስማት የሚገባቸው ቤተ ክርስቲያናቸው የምትነግራቸውን መሆን አለበት፡፡ ምክንያቱም «ጦር ከፈታው ወሬ የፈታው» እንዲሉ በወሬ የተፈቱ ብዙዎች ናቸውና፡፡ እስራኤል ዘሥጋ ምድረ ርስትን ከመውረስ የደከሙትና በእግዚአብሔር ላይ የነበራቸውም ተስፋ የጠወለገው፣ ዐሥሩ ሰላዮች ያወሩትን እምነት የጎደለው ወሬ እውነት ነው ብለው በመቀበላቸው ነበር፡፡ /ዘኁ.13. 28/፡፡ በአዲስ ኪዳንም ጌታችን ሞትን ድል አድርጎ በተነሣ ጊዜ አይሁድ «ደቀ መዛሙርቱ በሌሊት መጥተው ከመቃብር ሰርቀው ወሰዱት» ብለው አስወርተው ነበር፡፡ ይህም ወሬ መግደላዊት ማርያምን አሳምኗት ስለነበረ ከአንዴም ሦስት ጊዜ ጌታን ከመቃብር ወስደውታል እስከ ማለት ደርሳለች፡፡ /ዮሐ. 20.2-13፤15/፡፡ ጥንትም አዳምና ሔዋን ከእግዚአብሔር የተጣሉት የሰይጣንን ወሬ እውነት ነው ብለው በመቀበላቸው ነበር፡፡ /ዘፍ.3.4/፡፡ ምክንያቱም የሐሰት ወሬ ከዲያብሎስ ነው፤ የሐሰት አባት እርሱ ነውና፡፡ /ዮሐ.8.44/፡፡ በእምነት መድከም በመጀመሪያ ሥርዓትን ትውፊትን ያስንቀናል፡፡ በሃይማኖት ለሚኖር ሰው ይህ ደግሞ አግባብ አይደለም፡፡ እንግዲህ ይህንን ሁሉ አውቀን በጊዜውም አለጊዜውም በሃይማኖት በምግባር ጸንተን ልንገኝ ይገባል፡፡ በእምነታችን እንድንጸና ምክንያት ሳናበዛ እምነታችንን ከሚያዳክሙ እኩይ ተግባራት በመራቅ እምነትን የሚያጠናክሩትን በጎ ተግባራት ሁሉ መያዝ አለብን፡፡ «በዓመፀኞች ስሕተት ተስባችሁ ከራሳችሁ ጽናት እንዳትወድቁ ተጠንቀቁ» እንደተባለ በማንም ሳንወሰድ የቅዱሳን አባቶቻችንን ሃይማኖት ከምግባር አስተባብረን ልንይዝ ይገባናል፡፡ /2ጴጥ.3.17/፡፡
5. ሥጋዊ መከራን መፍራት
5. ሥጋዊ መከራን መፍራት
ሥጋዊ መከራን መፍራት እምነትን ያደክማል፡፡ ይህም ለዘለዓለም ሞት አሳልፎ ይሰጣል፡፡ /ራዕ.21.7/፡፡ እግዚአብሔር ግን የፍርሃትን መንፈስ አላሳደረብንም /2ጢሞ.1.7/፡፡ ለሥጋ ፍላጎት መገዛት ማለትም ለዝሙት፣ ለገንዘብና ለሥልጣን ወዘተ መገዛትም እምነትን ያዳክማል፡፡ /1ነገ.11.1፤ ማቴ.19.22፤ ዮሐ.5.4-9፤ ዕብ.4.4፤ 2ጴጥ.2.15፤3ዮሐ.10፤ ራዕ.2.14/፡፡ ምድራዊ ችግርም ሲያዩት የሚያልፍ ስለማይመስል እምነትን ያዳክማል፡፡ ጌዴዎን «ጌታዬ ሆይጠ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ከሆነ ይህ ነገር ሁሉ ለምን ደረሰብን)» ያለው በምድራዊ ችግር ብዛት እምነቱ ደክሞ ስለነበር ነው፡፡ ቅዱሳን ሐዋርያትም የማዕበሉን ኃይል አይተው «ጌታ ሆይ ስንጠፋ አይገድህምን)» ያሉ ለዚህ ነው፡፡ /ማር.4.35/፡፡ ከሁሉም በላይ ደግሞ ልንጠነቀቅ የሚገባው ሰይጣን እንዳያታልለን ነው፡፡ ምክንያቱም ቅዱስ ጳውሎስ እንደተናገረው የብርሃን መልአክ እስከሚመስል ድረስ ራሱን ይለውጣልና፡፡ /2ቆሮ.11.14/፡፡ እንዳለ፡፡ ምትሐታዊ የሆኑ ድንቅ ምልክቶችንም ያደርጋልና፡፡ /2ተሰ.2.3-9/፡፡ ሌላው ደግሞ ቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ ካለው ነገር የምንጠራጠርበት ምንም ዓይነት ነገር መኖር የለበትም፡፡ ምክንያቱም ዛሬ በዓይነ ሥጋ ብቻ በመመልከት ጥቃቅን መስለው በሚታዩን ነገሮች መጠራጠር ከጀመርን ነገ ደግሞ የእግዚአብሔርን አዳኝነት እስከ መጠራጠር እንደርሳለንና ነው፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር